የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ

የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ፡፡

አባላቱ ዛሬ ቃለ መሀላ እንደሚፈፅሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከመሃላው በፊት ሀገሪቷን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊው መንግስት ከሲቪል ተወካዮች በሁለት በልጦ አባል መርጦ አዘጋጅቷል፡፡

አባላቱም በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

ሱዳን ሰላም አጥታ ለበርካታ ወራት ስትታመስ ከቆየች በኋላ ለህዝቡ ጥያቄ የመጨረሻ እልባት መፍትሄ ሰጭ የተባለለት የስምምነት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡

የሀገሪቷ የአስተዳደር አካል ከወታደራዊው አገዛዝ ይልቅ ህዝባዊ አካል ሀገሪቱን ሊያስተዳድር ይገባል የሚል ሀሳብ በተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ሲመራና ሲራመድ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ ሀሳብ በገዥው ወታደራዊው መንግስት እና በህዝብ መካከል ከፍተኛ መተራመስ በመፈጠሩ ከ127 በላይ ሱዳናዊያንም ሞት እና ለባርካቶች አካላቸው ጉዳት ምክንያት ሆኗል፡፡ ሱዳን ሰላም እንድታገኝ እና በገዢው አካል መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ጥረት ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡

በስተመጨረሻም ሁለቱ አካላት ስምምነት ላይ ደርሰው ዛሬ መቋጫዉን ሊያገኝ ስልጣን ላይ ያለው ወታደራዊው መንግስት እና የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት የስልጣን ክፍፍል ሊያደርጉ የሉዓላዊ ምክር ቤት አባሎቻቸዉን መርጠው አዘጋጅተዋል፡፡

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት ወታደራዊው መንግስት ከሲቪሊያኑ በሁለት ከፍ ብሎ ሰባት በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸዉን አባሎቻቸዉን መርጠዋል፡፡

በዘመነ አልበሽር ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ያን ያህል ነበር፡፡ ከዚህ አካሄድ ለየት ባለ መልኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመረጧቸው አባላቶቻቸው ውስጥ ሴቶችን አካተዋል ነው የተባለው፡፡

ሁለቱ አካላት ሰልጣን መጋራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ቅዳሜ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ የመጨረሻ መሃላ ሊፈፅሙ የምክር ቤቱ አባላቶቻቸዉን አዘጋጅተዋል፡፡

አባላቶቹ በምክር ቤቱ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ቢሆንም ትልቁ ኃላፊነታቸው ለካቢኒው የሚሰሩ ነው የሚሆነው፡፡ ሱዳን አጥታ ለነበረው ሰላም እና ህዝቡ ሲያነሳ ለነበረው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ነው የተባለው ይህ ስምምነት ዛሬ ላይ በርካታ ሱዳናዊያን በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ጎዳና እንዲወጡ ምክኒያት ሆኗቸዋል፡፡ ደስታቸዉን ለመግለጽ እና የፊርማ ስምምነቱን ለማክበር ሲባል፡፡

ሁለቱ አካላት ዛሬ የመጨረሻ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙ ሲሆን፣ በስምምነታቸውም መሰረት ወታደራዊው ሽግግር መንግስት ለ21 ወራት ስልጣን ላይ የሚቆይ ሲሆን የሲቪሉ አካል ደግሞ ለሚቀጥሉት 18 ወራት ስልጣን በመጋራት በጋራ ሱዳንን ያስተዳድራሉ፡፡

(ምንጭ፡-ሚድል ኢስት እና አልጄዚራ)