ሞቃዲሾ አዲስ ከንቲባ አገኘች

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የቀድሞውን የጦር አበጋዝና የመንግሥት ሚኒስትር የነበሩት ኦማር መሐመድን  የሞቃዲሾ ከንቲባና የባዲር ግዛት አስተዳደሪ አድርገው ሾመዋል።

ሹመቱ ባለፈው ወር በአጥፍቶ ጠፊዎች ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ ከንቲባ አብዱራህማን ኦማር ኦስማንን ለመተካት መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዲሱ ከንቲባ ኦማር መሐሙድ መሐመድ እ.አ.አ 2004 ላይ በተመሠረተው የሽግግር መንግሥት ውስጥ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ከመሆናቸው አስቀድሞ ሞቃዲሾ ውስጥ የጦር አበጋዝ ነበሩ።

እ.አ.አ እስከ 2009 ድረስም በሚኒስትርነት አገልግለዋል።

ኦማር መሐመድ ለሞቃዲሾ ከንቲባነት የተመረጡት በመንግሥት ውስጥ ባላቸው ልምድ እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊነት ማስቀጠል የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።