ሱዳን  አዲሱ  ካቢኔዋን  በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ይፋ አደረገች

ሱዳን የሽግግር መንግስት ካቢኔ ማዋቀሯን ጠቅላይ ሚኒስትር አብድላ ሃምዶክ አስታውቀዋል፡፡

የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የተቋቋመ የመጀመሪያ ካቢኔ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አዲሱ ካቢኔ 18 ሚኒስትሮችን ያካተተ ሲሆን ፤ ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ሴቶች ናቸው፡፡

ይሁንና የመሰረተልማትና ትራንስፖርት እንዲሁም እንስሳትና ዓሳ ሃብት ሚኒስትሮች ስም እስካሁን ይፋ አልሆነም፡፡

የቀድሞው የዓለም ባንክ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ኢብራሂም ኤልባድዊ የገንዘብ ሚኒስትር በመሆን ተሰይመዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት የሱዳን መንግስት ካቢኔውን በማሳወቁ እና በተለይም የሴቶች የካቢኔ ተሳትፎን ለማሳደግ የደረሰበትን ውሳኔ  አድንቀዋል፡፡