የአብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም  የ15 ዓመት እስር ተበየነባቸው

የአልጀሪያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም ላይ የ15 ዓመት እስር አስተላልፏል።

በመንግስት ላይ ሴራ በመጎንጎን እና የሀገሪቱን ጦር ሚና ዝቅ አድርገዋል በሚል የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም ሰይድ ቡተፍሊካ  እስሩ ተላልፎባቸዋል፡፡

በተባባሪነት የተጠረጠሩ ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም ተማሳሳይ እስር ተበይኖባቸዋል፡፡

ለእስር የተዳረጉት ሁለት የሀገሪቱ የቀድሞ የደህንነት መስሪያ ቤት አለቃዎች እና እንድ የፓለቲካ ፓርቲ መሪ ናቸው፡፡

ሰይድ ቡተፍሊካ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊክ በስትሮክ ህመም ከተጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ከጀርባ በመሆን የፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን በመያዝ ሀገሪቱን ሲመሩ መቆየታው ይታወሳል፡፡

ለእስር የተዳረጉትም በሀገሪቱ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅና የሀገሪቱን ጦር አለቃ አህመድ ጋይድ ሳላህን ከስልጣን ለማንሳት አሲረዋል በሚል ነበር።

ምንጭ፦አልጀዚራ