በአፍሪካ የውሃ ሃብት አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በናይሮቢ እየተካሄደ ነው

በአፍሪካ የውሃ ሀብት ዘላቂ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ ተጀመረ።

በጉባኤው ላይ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ነው።

ጉባኤው የአህጉሪቱን የሰማያዊ ኢኮኖሚ በዘላቂነት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የዓለማችንን የውሃ አካላት ለሰብዓዊ ፍጡር አገልግሎት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ይመክራል ነው የተባለው።

በዚህ ጉባኤ ላይ ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።(ምንጭ:የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)