በዲሞክራቲክ ኮንጎ በደረሰ የባቡር አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ በደረሰ የባቡር መገልበጥ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

ከአደጋው ሰለባዎች መካከል አብዛኞቹ ህጻናት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከ30 የሚበልጡ ሰዎች ላይ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

ካሳይ በምትባለው ግዛት ውስጥ በደረሰው በዚህ አደጋ በጭነት ባቡር ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ናቸው ጉዳት የደረሰባቸው።

ፖሊስ እንዳለው በርካታ የባቡሩ ፉርጎዎች ወንዝ ውስጥ በመግባታቸው የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተሰግቷል።

አደጋው በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአካባቢው የደረሰ 3ኛው አደጋ ነው ተብሏል።

ኮንጎ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ ባቡሮች በ1960ዎቹ የተሰሩ ሲሆን የባቡር ሃዲዶቹም ተገቢው ጥገና አልተደረገላቸውም ነው የተባለው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)