በሰሜንና በምስራቅ አፍሪካ ከ52 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን የዓለም የምግብ ድርጅት አስታወቀ

በሰሜንና በምስራቅ አፍሪካ ከ52 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን የዓለም የምግብ ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

ለከፍተኛ ረሃብ ከተጋለጡት መካከል 33 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎች ሲሆን ህፃናት በከፋ ሁኔታ የጉዳቱ ሰላባ ናቸው ተብሏል፡፡

በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በሶሪያና በየመን ለዓመታት የዘለቀው ጦርነት ችግሩን እንዳባባሰው ነው የተነገረው፡፡

በሰሜንና በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ግጭቶችና የህዝቦች አለመረጋጋት በቀጠናው አገራት የምግብ እጥረት መፍጠሩን የድርጅቱ ኃላፊዎች ጠቁመዋል፡፡

ከግጭቶቹ በተጨማሪ በተጠቀሱት አካባቢዎች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የተፈጥሮ ሀብት መመናመንና የአየር ንብረት ለውጥ ለረሃቡ መባባስ ዓይነተኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡

(ምንጭ፡- ተ.መ.ድ)