ሶማሊያ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን ሰረዘች

በሶማሊያ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናዎችን በመውሰድ ላይ እያሉ ከአንድ የፈተና መስጫ ማዕከል ፈተና ተሰርቆ በማህበራዊ ሚዲያ በመውጣቱ አገሪቱ ፈተናዎቹን ሙሉ ለሙሉ ሰርዛለች፡፡

የሶማሊያ የትምህትርት ሚኒስትር አብዱላሂ ጎዳህ በአገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው ፈተናው በይፋ መሰረዙን አረጋግጠዋል፡፡

የተሰረዘው የብሄራዊ ፈተና መስጫ ቀን ዳግም በተያዘው ወር መጨረሻ ባሉት ቀናት እንዲካሄድ መወሰኑና የማህበራዊ መገናኛ አውታሮችም በፈተና ቀናት እንደሚዘጉ በመገለጫቸው አመልክተዋል፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)