የኡጋንዳ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ጭና የነበረች ጀልባ ሰመጠች

50 የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና ደጋፊዎቻቸውን ጭና ከምእራብ ኡጋንዳ የተነሳችው ጀልባ በአልበርት ሃይቅ መስመጧ ተሰማ።
እስከ አሁን የዘጠኝ ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን የጀልባዋ ተሳፋሪዎች በሙሉ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ተፈርቷል።
የአይን እማኞች እንደሚሉት ከአቅም በላይ መጫንና መጥፎ የአየር ፀባይ ለጀልባዋ መገልበጥ ምክንያት ነው።
የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከሌላ አካባቢያዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ እየተጓዙ እንደነበር ተውቋል፡፡
አደጋው ጀልባዋ ጉዞ በጀመረች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደተከሰተም ተገልጿል።