ኬኒያ በኢንቨትመንት ፍቃድ ስም ሲያቋምሩ የነበሩ 17 የውጪ ዜጎችን ከሀገሯ አስወጣች

ኬኒያ በኢንቨትመንት ፍቃድ ስም ሲያቋምሩ የነበሩ አስራ ሰባት የውጪ ዜጎችን ከሀገሯ ማስወጣቷ ተገልጿል፡፡

አስራ ሰባት የወጪ ሀገራት ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ከተሰጣቸው የኢንቨትመንት ፍቃድ ውጪ በማቋመር ስራ ተሰማርተው መገኘታቸውን ተከትሎ ኬኒያን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

ውሳኔው የተላለፈው ለረጅም ጊዜ ከተከናወነ ዳሰሳ  መሆኑን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ተቋም አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ለውጪ ሀገራት የተሰጠው የኢንቨስትመንት ፍቃድ ዳሰሳ ግኝት እንደሚያመለክተውም አስራ ሰባቱ ግለሰቦች አቋማሪ ድርጅት ከፍተው ተኝተዋል፡፡

ከነዚህአቋማሪዎች ውስጥ ቻይናውያን የቱርክ እና የስፔን ዜግነት ያላቸው እንደሚገኙበት ነው የተገለጸው፡

በኬኒያ በአሁኑ ሰዓት 30 የሚጠጉ ህጋዊ አቋማሪ ድርጅቶች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን በስራ ላይ ያሉት ግን ጥቂቶቹ መሆናቸውን መረጃው አስነብቧል፡፡

የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ባለስልጣን 90 በመቶ አቋማሪ ድርጅቶች የውጪ ሀገራት ዜጎች መሆናቸውን ጠቅሶ ይህም በርካታ የውጪ ምንዛሪ በህገወጥ መንገድ ከሀገሪቱ እንዲወጣ ምክኒያት መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ህገወጥ የቁማር ተግባር ከፍ ሲልም የኬኒያን ባህል እና ኢኮኖሚያዊ ክፉኛ እየጎዳው ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡

የአቋማሪ ድርጅቶች ተቆጣጣሪ አካል እንዳስታወቀው በኬኒያ 7 ቢሊዮን ሽልንግ በወር ከዚህ ዝርፍ ገቢ እንደሚያገኝ የገለጸ ሲሆን በአመትም እስከ 100 ቢሊዮን ሽልንግ ይገኛል ሲል አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ከስፖርት አቋማሪዎች በአመት 20 ሚሊዮን ዶላር በቁማር እንደሚዘዋወር እና ይህም በፈረንጆቹ 2020 ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ድርጅቱ አክሎ ገልጿል፡፡

መረጃው አክሎም ኬኒያን ከደቡብ አፍሪካና ናይጄሪያ ቀጥሎ ሶስተኛ የቁማርተኞች ሃገር መሆኑኗን አትቷል፡፡በገቢ ደረጅ ግን ቀዳሚዋ ናት ብሏል፡፡

ለዚህ ደግሞ የስፖርት ቁማሮች በኢንተርኔት እና በስማርት ስልኮች የታገዘ መሆኑ አበርክቶ እንዳለው ተገልቷል፡፡

የኬኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ አደረጉት ባለው ዳሰሳ መሰረት በርካታ ወጣቶችን ወደ ቁማር የሚጋብዘው ሁነኛ ምክኒያት ድህነት መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

/ምንጭ:- ኔሽን /