ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጽንፈኝነትን እንዲዋጋ ጥሪ አቀረቡ

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጽንፈኝነትን በመዋጋት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ታሪካዊ የተባለለትንና ያልተጠበቀ ጉብኝት በአንድ መስጊድ ካደረጉ በኃላ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ኬንያታ ትላንትና ማታ ጃሚያ መስጊድ ተገኝተው የረመዳን ጾም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ባከበሩበት ወቅት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጽንፈኝነትን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ወንጀል እና ጽንፈኝነትን ለመከለካል ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአገሪቱ የትኛውም ዓይነት ጥቃት ቢፈፀም ጥቃት አድራሾቹ ሙስሊም ወይም ክርስቲያን ሳይሆኑ ወንጀለጆች ናቸው ብለዋል ፡፡

ስለሆነም እንዚህ ወንጀለኞች የሙስሊሙም ሆነ የክርስቲያኑ ጠላቶች በመሆናቸው በጋራ ልንዋጋቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ኬንያ መሰረቱን ሶማሊያ ባደረገው አሸባሪው ቡድን አልሸባብ ተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶባታል፡፡
ከጥቃቶቹ መካከል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 በጋርሽያ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው እና ለ150 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የሽብር ጥቃት ተጠቃሽ ነው ዘገባዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡