ደቡብ ሱደናዊ ስደተኛ የዛፍ ችግኞችን በመትከል ለአከባቢዉ ጥበቃ እያደረገ ነው

በኡጋንዳ ከሚኖሩ 1.2 ሚሊዮን ስደተኞች መካከል አንዱ የሆነው የ32 ዓመቱ ቢዳል አብረሃም በደቡብ ሱዳን ባጋጠመው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የልጁን እናት ይዞ ለሦስት ጊዜ ወደ ኡጋንዳ ተሰዷል።

በእያንዳንዱ የስደት ጉዞ ታዲያ በሚመላለስበት ወቅት በየመንገዱ ጥቂት ዛፎችን ይመለከት ነበር።

“ለመጀመሪያ ጊዜ ስመጣ ብዙ ዛፎች ነበሩ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ስመጣ ቁጥራቸው ከበፊቱ ያነሱ ዛፎች አየሁ። ለሦስተኛ ጊዜ ስመጣ ግን በተበታተነ ቦታ በጣም አነስተኛ ዛፎች ነበሩ“ ብሏል ቢዳል።

ቢዳል በስደት ምክንያት ከሀገሩ ቢሰደድም በኡጋንዳ ችግኞችን ከመትከልና ከመንከባከብ ምንም አላገደዉም፤ እንዳዉም ሌሎች ስደተኞችን ልምዱን እንዲጋሩ አድርጓል፡፡

"ዛፎች ሕይወት ያላቸው በመሆናቸው ችግኞችን መትከል አስፈላጊ ነው" በማለት የሚናገረው ቢዳል "ዛፎች ለእኛ እና ለእንስሳት ጥላ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ተጨማሪ ንፁህ አየር ይሰጣሉ::

ለከሰል ብለን ዛፎችን እንቆጥራለን ስለዚህ በየጊዜው ዛፎችን መትከል አስፈላጊ ነው። አንድ ቀን ወደ ደቡብ ሱዳን እንመለሳለን ይህን ቦታ መጀመሪያ እንዳገኘነው ማድረግ እንችላለን "በማለት ተናግሯል

በየቀኑ ለአንድ መቶ ሰዎች የዛፍ ችግኞችን እንዲተክሉ ጥሪ ብታደርግ ከ10 እስከ 20 ሰዎች ምክሩን ተቀብለው ተግባራዊ ያደርጋሉ፤ይሁን እንጂ ተስፋ ሳንቆርጥ ጥረታችንን እንቀጥላለን ብሏል የአከባቢ ጥበቃ ተሟጋቹ ስደተኛ ቢዳል፡፡

በእርግጥ ይላል ቢዳል ባለንበት አከባቢ ለአከባቢ ጥበቃ ምንም ግድ የሌላቸው አንዳንድ ግለሰቦች አሉ፤ እየመጡ ዛፎችን የሚቆርጡ፤ ምንም እንኳን የአከባቢው ማህበሰረሰብ በተወሰነ መልኩ የመቆርቆር ስሜት ቢያሳይም አልፎ አልፎ ግን እንጋጫልን፡፡

ዛፎች እያደጉ ሲሄዱ በካይ ጋዝን ከአየር በመውሰድ በዛፎችና በአፈር ውስጥ ካርቦን በማከማቸትና ኦክስጅንን ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ የአየር ንብረት ለውጥን ይከላከላሉ።

አንድ ዛፍ በየዓመቱ እስከ 48 ፓውንድ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ድረስ ሊወስድ ይችላል ።

ዛፉ 40 አመት በሚደርስበት ጊዜ አንድ ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከከባቢ አየር ማስወገድ ይችላል ነው የተባለዉ መረጃዉ ዩኤንኤችሲአር ነዉ፡፡