ኬንያ በመጪዎቹ ቀናት ጠንካራ ንፋስ ሊያጠቃት እንደሚችል ተጠቆመ

ከእሁድ ጀምሮ ጠንከር ያለ ንፋስ  በኬንያ ጠረፋማ አካባቢዎች ሊከሰት እንደሚችል የኬንያ ሚቲዎሮሎጂ ተቋም አሳስቧል፡፡

በተለይም በመጪው ሰኞ የንፋሱ ፍጥነት ይበልጥ ሊጨምር እንደሚችልም ነው የሀገሪቱ የሚቲዎሮሎጂ ባለሙያዎች ያስጠነቀቁት፡፡

በዕለቱ የንፋሱ ፍጥነት ከ25 ማይል በሰከንድ ሊሆን እንደሚችልም ትንበያ አስቀምጠዋል፡፡

ይህ ችግር በመቺዎቹ አራት እና አምስት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተተነቤየ ሲሆን÷ በኬንያ ከፍተኛ የሥጋት ቀጠና የተባሉ አካባቢዎችም ላሙ፣ሊሊፊ፣ሞምባሳ፣ ክዋሌ እና ታይታ ታቬታ ናቸው፡፡  

በመሆኑም በማኩኒ፣ ማቻኮስ እና ደቡባዊ ካጃዶ የሚገኙ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

(ምንጭ፦ ሲጂቲኤን)