ኢቦላ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ውጭ አለመከሰቱን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

ድርጅቱ ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ኢቦላ በዲሞክራቲክ ኮንጎ መከሰቱና መስፋፋቱ ቢታወቅም እስከዚህ ሳምንት ድረስ ግን በሌሎች አጎራባች አገራት አለመከሰቱን አስታውቋል።

በአንፃሩ እስከ ሐምሌ አጋማሽ ድረስ ብቻ ግን 165 የኢቦላ ቫይረስ በተለያዩ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ግዛቶች መከሰቱን የአለም ጤና ድርጅት አመልክቷል።

ኢቦላ በተቀሰቀሰባት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለው የችግሩ አሳሳቢነት እጨመረ በመምጣቱ ቀውሱን የአለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ የጤና ስጋት በሚል ድንጋጌ አሳልፎ እየተንቀሳቀሰም ይገኛል።

በማዕከላዊ አፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ እ.ኤ.ኤ በ2014 በምዕራብ አፍሪካ ከተከሰተው በመቀጠል በከባድነቱ የሚቀመጥ ነው።

(ምንጭ፡- ሲጂቲኤን)