ሩዋንዳ በትምህርት የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ ሆናለች -ተመድ

በሩዋንዳ የተዘረጋው የትምህርት መርሀ ግብር የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ እየሆነ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

የዓለም ወጣቶች ቀን በዚህ ሳምንት በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል፡፡

ወጣቶችን በትምህርት በማብቃት ማህበራዊ ለውጡን ማገዝ በሚለው መርህ መሰረት ሩዋናዳ  ይበል የሚያሰኝ ለውጥ ስለማስመዝገቧ ተዘግቧል፡፡

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማህበራዊ፤ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ረገድ ማስፋት ዓለም እየገጠማት ላለው ችግር ሁነኛ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ትምህርት ዋነኛ የአመለካከት ለውጥ መሳሪያ መሆኑን ተከትሎም ሩዋንዳውያን ወጣቶች የለውጡን ፈር እየተከተሉ ስለመሆናቸው  ነው የሀገሪቱ መንግስት ይፋ ያደረገው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዜጎች እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ውስጥ እንደሚገኝ መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን፤ ከዚህ ውሰጥ 226 ሚሊየኑ በአፍሪካ  ይገኛሉ፡፡

ሩዋንዳም 60 በመቶ ዜጎቿ እድሜያቸው ከ 25 በታች መሆኑን ተከትሎ በትምህርት እንዲዘልቁ በማድረግ በኩል አበክራ በመስራቷ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዪኒስኮ እውቅና ችሯታል፡፡

ባሁኑ ሰዓት ከዓለማችን 262 ሚሊዮን ህጻናትና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት ማመላከቱን ተከትሎ ሩዋንዳ ፍታዊ የትምህርት ተደራሽነትን ማሰካቷ ወደኋላ ለቀሩት ሀገራት ተምሳሌት እንድትሆን አሰችሏታል፡፡

ከሁለት አመታት አስቀድሞ ይፋ ያደረገቸው የሰባት አመት የትምህርት ማሻሻያ ስትራቴጂ ለውጤቱ እንዳበቃት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ እየተመዘገብ ባለው ውጤት መሰረትም ተመድ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው ሲል ዘ ኒው ታይምስ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡