ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ዘጋች

ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ለመዝጋት የተገደደችው በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ነው።

ባለፈው ሳምንት እሁድ የጀመረው በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት  ቀጥሎ የብዙዎች ንብረት ተዘርፏል ፤ ድብደባ ተፈፅሟል፡፡

ድርጊቱን የናይጀሪያ መንግሥት ያወገዘው ሲሆን፤ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው  ተግባሩን አሳፋሪ ብለውታል።

በናይጄሪያ መዲና አቡጃ የሚገኘውን የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ለመዝጋት የተገደዱት በኤምባሲው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ከደረሰባቸው በኋላ እንደሆነ ሚኒስትሯ ለሮይተርስ መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡