የሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ዚምባቡዌ ተሸኘ

ከቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ሀገሩ ዚምባቡዌ በአውሮፕላን ተሸኝቷል።

ላለፉት ወራት በሲንጋፖር  ሕክምናቸውን ሲከታተሉ  የቆዩት ፕሬዚዳንቱ በ95 ዓመታቸው ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡

የቀብር ስነስርዓታቸውም የፊታችን እሁድ የሚፈፀም ሲሆን፤  ከዚህ አስቀድሞ 60 ሺህ ተመልካቾችን ያስተናግዳል በተባለ ስታዲየም ይፋዊ የስንብት  ይከናወናል ተብሏል፡፡

የቀብሩ ቦታን በተመለከተ ግን እስካሁን ከስምምነት አለመደረሱም ነው ቢቢሲ በዘገባው  ያመለከተው፡፡

በወቅቱ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስተዳደር እና በሙጋብዌ ቤተሰቦች መካከል  ቀብሩ የት ይፈፀም በሚለው ጉዳይ ላይ ከመግባባት አልተደረሰም ተብሏል፡፡