የቀድሞው የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት አብዲን ቢን አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ዚን ኢል አብዲን ቢን አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት በ83 ዓመታቸው በስደት እየኖሩ ባሉበት ሳዑዲ አረቢያ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡

ቱኒዚያን ለ23 ዓመታት የመሩት ቢን አሊ ሀገሪቱ እንድትረጋጋ እና እንድትበለጽግ አድርገዋል ተብለው በብዙዎች ይነገርላቸዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2011 በሀገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በአረብ ሀገራት ሁሉ ተቀጣጥሎ ለእርሳቸውና ለሌሎች የአረብ ሀገራት ባለስልጣናት የስልጣን ማክተሚያ ምክንያት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የቢን አሊ የቀብር ስነስርዓት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚፈፀም ጠበቃቸው ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግሯል፡፡