በኬንያ በአንድ ትምህርት ቤት በደረሰ የመደርመስ አደጋ የሰባት ህፃናት ህይወት አለፈ

በኬንያ በአንድ ትምህርት ቤት በደረሰ የመደርመስ አደጋ የሰባት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የሚገኝ በእንጨት የተሰራ የመማሪያ ክፍል በመደርመሱ አደጋው መከሰቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ከተጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ አደጋው በመከሰቱ ውጤቱ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ከአደጋው በኋላም የትምህርት ቤቱ መግቢያ በሰው በመጨናነቁ የነፍስ አድን ስራው ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡

ፕሪሽየስ ታለንት ቶፕ የተሰኘው የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሞስስ ኒራንጉ  በአቅራቢያው እየተከናወና ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ቀበራ ስራ አደጋው እንዲከሰት አድርጓል ሲሉ ውንጀላ አቅርበዋል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ህጻናት በተጨማሪ በርካታ ህጻናት በእንጨት ክምሩ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

የኬንያ ቀይ መስቀል ድርጅት ከአደጋው በህይወት የወጡ ህፃናትን ወደ ኬንያታ ሆስፒታል ማጓጓዙን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡