ጣሊያን የሮድ ኤንድ ቤልት መርሃ ግብርን ለመቀላቀል የሚያስችላትን የመግባቢያ ሰነድ ከቻይና ጋር ተፈራረመች

ሁለቱ ሀገራት በመርሃ ግብሩ አማካኝነት የመሰረተ ልማት ግንባታን ለማቀላጠፍ፣ ትብብራቸውን ለማጠናከርና ስልታዊ አጋርነትን ለማስፋት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

ጣሊያን ማዕቀፉን በመጠቀም ከእስያ መሰረተ ልማት መዋዕለ ንዋይ ባንክ ጋር በመተባበር የህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንሰራለን ብላለች፡፡

ቻይናና አውሮፓ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን የኢንቨስትመንት ኘሮጀክቶች በመጠቀም ለመተባበር የሚያስችል ድርድር እየተካሔደ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጣሊያን በአንዱስትሪ የበለፀጉ የቡድን ሰባት ሀገራት መካከል ለሮድ ኤንድ ቤልት መርሃ ግብር ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያም ሀገር ሆናለች፡፡

በዋሽንግተንና በብራስልስ አካሔዷ ያልተወደደላት ጣሊያን በኃይል ልማት፣ በብረታ ብረትና በጋዝ መስመር ዝርጋታ መስኮች ከቻይና ጋር ለመተባበር የሚያስችላትን ስምምነት ፈርማለች፡፡ (ምንጭ፡- ቢቢሲ)