አሜሪካ ለኳታር 24 የአፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ልትሸጥ ነው

አሜሪካ 3 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ 24 አፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ለኳታር ልትሸጥ መሆኑን አስታወቀች።

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለኳታር ሄሊኮፕተሮችን ለመሸጥ የሚያስችለውን ስምምነት ማጽደቁ ተገልጿል።

ሆኖም የሽያጭ ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ያልተጠናቀቀ ሲሆን፣ ኮንግረሱ ጉዳዩን እንደሚመለከተው ነው የተገለጸው።

ሽያጩ በአሁኑ ወቅት የባህረሰላጤው ሃገራት በአጠቃላይ ያላቸውን የአፓቼ ሄሊኮፕተር ቁጥር በእጥፍ ያሳድገዋልም ተብሏል።

ከሄሊኮፕተር ሽያጩ በተጨማሪም ሞተሮች፣ ሚሳኤልና የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም የምሽት የእይታ መሳሪያዎችን ያካትታልም ነው የተባለው።

ኳታር ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የመጀመሪያው ዙር ኤ ኤች-64 ኢ አፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ከአሜሪካ መረከቧ የሚታወስ ነው።

(ምንጭ፡-አልጀዚራ)