የቻይና የተጨማሪ እሴት ታክስ ቅናሽ ዜጎቿን ተጠቃሚ ማድረጉ ተገለጸ

ቻይና ያደረገችዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቅናሽ የሃገር ዉስጥ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረጉ ተገልጸ፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ቅናሽን ተከትሎ የሀገሪቱ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ጫና እንደቀነሰላቸዉና በዚህም ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ይህ ደግሞ በተለይ በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፉ ላይ የሚታየዉን የታክስ ጫና ቀንሶታል ነዉ የተባለዉ፡፡ ቻይና ያደረገችዉ ተጨማሪ የእሴት ታክስ ቅነሳ በተለይም ቀደም ሲል በአነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን እድገት ያቀጭጭ እንደነበር ነዉ በዘገባዉ የተመለከተዉ፡፡

በሃገሪቱ ደቡባዊ ጉዋንግዶንግ ግዛት የሚገኘዉ የኬሚካል ኩባንያ በተደረገዉ የታክስ ቅነሳ ኩባንያዉ ባለፈዉ የሚያዚያ ወር ሪፖርቱ ከ14 ሚሊየን ዩአን በላይ ወይም ከ2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ ማዳኑን አስታዉቋል፡፡

የታክስ ጭማሪዉ መቀነሱን ተከትሎ አሁን ኩባንያዉ የፋይናንስ ጫናዉ በመቀነሱ በሌሎች የኢንቨስትመንት ሴክተሮች ለመሰማራት አቅም እንደሚፈጥርለት የኩባንያዉ የወጪ እና የገቢ ንግድ ዋና ስራአስኪያጅ ዩ ዶንግ ገልፀዋል፡፡

ሃገሪቱ የታክስ ቅናሽ ማድረጓን ተከትሎ በተለይም የአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከመጪዉ የሰኔ ወር ጀምሮ ቀደም ሲል 16 በመቶ የታክስ ክፍያ ሲከፍሉ የነበሩ ወደ 13 በመቶ ዝቅ የተደረገላቸዉ ሲሆን፣ 10 በመቶ ቫት ወይም ተጨማሪ እሴት ታክስ ሲከፍሉ የቆዩ ታክስ ከፋዮች ደግሞ 9 በመቶ ብቻ እንዲከፍሉ ይደረጋል ሲል የሃገሪቱ ገቢዎች ባስልጣን አስታዉቋል፡፡

የሃገሪቱ ገቢዎች ባስልጣን መረጃ እንደሚያሳየዉ ከ1500 የበላይ የሚሆኑ በጉዋንግዶንግ የሚገኙ ዡሃይ እና ዦንግሻን የሚገኙ የሃገር ዉስጥ ኢንተርፕተራይዞች ከመጪዉ ሰኔ ወር ጀምሮ በአጠቃላይ ወደ 190 ሚሊየን ዩአን የታክስ ቅናሽ ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡

በሰሜናዊ ምስራቅ የሚገኙ ከ4000 በላይ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም ባለፈዉ ወር ከከፈሉት 980 ሚሊየን ዩአን የታክስ ቅናሽ እንደሚደረግ ታዉቋል፡፡

በመጨረሻም ካለፈው ሚያዚያ ውር ጀምሮ የተተገበረዉ የታክስ ቅናሽ ባጠቃላይ በአመቱ መጨረሻ 225 ቢሊየን ዩአን ማለትም ወደ 33 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ሃገሪቱ የገቢዎች ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡ (ምንጭ፡-ሲጂቲኤን)