የኢራቋ ከተማን ከአሸባሪው አይ ኤስ ነፃ ለማውጣት የተጀመረው ዘመጃ ከታቀደው በላይ የፈጠነ መሆኑ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይደር አል አባዲ ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያያት፤ ወታደሮች ከታቀደው ጊዜ ቀደም ብለው ወደ ከተማዋ በፍጥነት እየተጠጉ ነው ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኩርድ ተዋጊዎች በምስራቅ እና ሰሜን ሞሱል መጠነ ሰፊ ዘመቻ መክፈታቸውን ተከትሎ በአሁኑ ጊዜም የኢራቅ ጦር በደቡብ በኩል ወደ ከተማዋ እየተጠጋ መሆኑን አመልክተዋል ፡፡
የሀገሪቱ ልዩ ሀይልም በአሁኑ ጊዜ ዘመቻውን ተቀላቅሏል ነው ያሉት።
ከተማዋን ከአሸባሪው ነጻ ለማድረግ የተጀመረው ዘመቻም ቁጥራቸው እስክ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚጠጋ ነዋሪዎች ባሉበት ነው የተከፈተው።
ይህን ተከትሎም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መኖሪያቸውን ለቀው በመሰደድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
ሞሱልን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣር ከ2014 ጀምሮ በአሸባሪው አስ ኤስ ቁጥጥር ስር ነው የምትገኘው-(ኤፍ.ቢ.ሲ)።