ፊደል ካስትሮ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የኩባ ፕሬዚዳንት በ90 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተገለጸ ።

ወንድማቸው ራወል ካስትሮ እንደገለጹት፥ ፊደል ካስትሮ  ትናንት  ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ፕሬዚዳንት ራወል በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ባስተላለፉት መልዕክት የቀድሞው መሪ የቀብር ስነ ስርአት በዛሬው  እንደሚፈፀም ተናግረዋል።

በአገሪቱ ብሄራዊ የሀዘን ቀን  እንደሚታወጅም ተገልጿል።

ደጋፊዎቻቸው ካስትሮ ኩባ ህዝቦቿን መመልከት እንድትጀምር አድርገዋታል ይሏቸዋል። በአንፃሩ ተቃዋሚዎችን የዴሞክራሲ  አፈናን ያካሄዳሉ  የሚል ትችት ያቀርባሉ ።

ከ50 አመታት በላይ ኩባን የመሩት ፊደል ካስትሮ እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 ለወንድማቸው ራወል ካስትሮ ስልጣናቸውን ማስረከባቸው ይታወሳል።

ከ58 አመታት በፊት ነበር ፊደል ካስትሮ እና ጓደኞቻቸው በመሩት የትጥቅ አመፅ የዚያ ዘመን የኩባ ወታደራዊ አምባገነን መሪ ፉላጂንሲዮ ባቲስታ አገዛዝ የተወገደው።

ካስትሮ ኮሚኒስቷን ሀገር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1959 እስከ 1976 በጠቅላይ ሚኒስትርነት፤ ከ1976 እስከ 2008 ደግሞ በፕሬዚዳንትነት መርተዋል።( ቢቢሲ)