45ኛው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራፕም ቃለ መሃላ ፈጸሙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራፕም 45ኛው የአሜሪካን ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጸሙ ።

ትራምፕ ትናንት ማታ የትራምፕን በዓለ ሲመት ለማክበር በርዕሰ ከተማ ዋሽንግተን በመቶ ሽህዎች የሚቆጠር ህዝብ ታድሟል።

የሪፓብሊካኑ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለቀጣይ 4ዓመታት አሜሪካን ለመምራት ዛሬ ዋይት ሃውስ ይገባሉ ነው የተባለው ።

በዓለ ሲመታቸውን ያከናወኑት ትራምኘ የተዋሃደችና ትልቋን አሜሪካ እንፈጥራለን ሲሉ አስታውቀዋል ፡፡

ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው ከመጀመሩ አስቀድሞ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ነገር ዛሬ ይጀመራል፤ እንቅስቃሴው ይቀጥላል ፤ ሥራው ይጀመራል ብለዋል።

በስነስርአቱ ላይ የዲሞክራቷ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሂላሪ ክሊንተንን ጭምሮ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችና አድናቂዎቻቸው ተገኝተዋል።

ትራምፕ ዕለቱን የጀመሩት ከባለቤታቸው ጋር በቤተ ክርስትያን ስነስርዓት በመታደም መሆኑን ነው የተመለከተው ፡፡

ከዚያ በኋላም ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ የቁርስ ግብዣ አድርገውላቸዋል ተብሏል ።

የትራምፕ ተቃዋሚዎች ህብረት ፈጥረው በዓለ ሲመቱ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ የሚያመሩ መንገዶችን በመዝጋት አከባበሩን ለማስተጓጎል ሙክራ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

በትራምፕ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ዋሽንግተን ውስጥ የተካሄደውን ግጭት ለማስቆም ፖሊስ ኬሚካሎችን መርጨቱን ነው የተገለጸው ።

የ70 ዓመቱ ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት በመምራት የመጀመሪያው በዕድሜ የገፉ መሪ ይሆናሉ ተብሏል ።