የተመድ ዋና ጸሐፊ በኢራቅ ውጊያ ለሲብሎች ከለላ ይደረግ አሉ

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተረዝ በኢራቅ የሞሱል ከተማን ለመቆጣጠር በቀጠለው ውጊያ የሚፋለሙት ወገኖች ለሲቭሎች ከለላ መስጠቱን ቀዳሚ ተግባራቸው እንዲያደርጉ አሳሰቡ።

የኢራቅ እና በዩኤስ የሚመራው ጥምር ኃይል ከአንድ ወር በፊት በእስላማዊው መንግሥት አንፃር ውጊያ በሚያካሂዱባት ሞሱል የሚገኙትበመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የሚገኙበት አሳሳቢ ጊዚያዊ ሁኔታ ይበልጡን እየከፋ እንዳይሄድ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸውም ኢራቅን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ጉተረዝ አክለው ተማጽነዋል።

ከ200,000 የሚበልጡ ውጊያውን በመሸሽ ሞሱልን ለቀው ወጥተዋል።

የዓለም መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጉተረዝ በመዲናይቱ ባግዳድ ከኢራቅ ፕሬዚደንት ፉዋድ ማሱም፣ ከምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሳሊም አል ጁብሪ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም አል ጃፋሪ ጋር ሐሳብ ተለዋውጠዋል።

ምንጭ -www.DW.com