በአሜሪካ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ የሚገድቡ ህጎች ተግባራዊ መሆን ቁጣን ቀሰቀሰ

በአሜሪካ አዲሱ የግዛቶች ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና ተቃውሞን ለመግለፅ አደባባይ መውጣትን የሚገድቡ ህጎች ተግባራዊ መሆን ቁጣን ቀስቅሰዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት አጣሪ ባለሙያዎች ማኢና ኪአኢ እና ዴቪድ ካዮ እንደገለጹት፤ ሀሳብን በነፃነት መግለፅና ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ መከልከል ከዓለም ዓቀፍ ሰብአዊ መብት መርሆ ጋር ይጋጫል፡፡

አዲሱ የግዛቶቹ አካሄድ የሀገሪቷ ህገ መንግስት ምሰሶ የሆነውን ሀሳብን በነፃነት መግለፅ መብት እንደሚፃረር ባለሙያዎቹ አስገንዝበዋል፡፡

ይህ እጅግ አሳሳቢና ፀረ ዲሞክራሲያዊ አካሄድ በሪፐብሊካን ፓርቲ በሚመሩ 19 ግዛቶች መተግበራቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት አጣሪዎች ገልፀዋል፡፡

ይህን መሰሉ አካሄድ በጊዜ ሊታረም እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከምርጫ ቅስቀሳ እስከ ፕሬዚዳንትነት መንበራቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና አስተዳደራቸው የዓለምን ህዝብ በብዙ መልኩ ማስደመማቸውን ቀጥለዋል፡፡

አሁን ደግሞ አሜሪካ ጠበቃ ነኝ በምትለው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት መወቀስ ጀምሯል ነው የተባለው ፡፡

ከአፍሪካ አሜሪካውያን ‹‹መብት ይከበርልን›› እንቅስቃሴ እስከ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾች፤ ከአሜሪካ ነባር ህዝቦች እንቅስቃሴ እስከ ሴቶች እንቅስቃሴ፤ አሜሪካውያን በየፈርጁ ተቃውሞዎቻቸውን በሠላማዊ መንገድ እየገለፁ ይገኛል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ በሚያስተዳድራቸው እንደ ኢንዲያና፣አርካንሳ፣ፍሎሪዳ፣ጆርጂያ፣አይዋ፣ ሚቺጋን እና ሚዞሪ ባሉት ግዛቶች ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብታቸውን እንዳይተገብሩ አዲሶቹ ህጎች እንቅፋት ሆነዋል ይላሉ-ባለሙያዎቹ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በኮሎራዶ፣በሰሜን ዳኮታ እና ኦኮሃልማ ሊተገበሩ የታሰቡት አዲሶቹ ህጎች  በአካባቢው ያሉ ዜጎች መንግስታቸው በአካባቢ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዳይቃወሙ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ለአልጀዚራ ገልፀዋል፡፡

በሰሜን ዳኮታ በበብዙ ቢሊዮን ዶላር ሊገነባ የታሰበውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ግንባታ በመቃወም በቦታው ላይ ድንኳን ተክለው ቅሬታቸውን የሚገልፁ ዜጎችን ካምፕ የሀገሪቷ የፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ጥሰው መግብታቸውንና በሚዞሪ ግዛት ሊተገበር የታሰበው ህግ እንደማሳያ ይጠቅሳሉ፡፡

በሚዞሪ ሊተገበር የታሰበው ህግ የትራፊክ ፍሰትን በማስተጓጎል ብቻ ለሰባት ዓመት ሊያሳስር እንደሚችል አልጀዚራ በዘገባው አመልክቷል፡፡

አርታኢ -በሪሁ ሽፈራው