በሶሪያ የኬሚካል ጥቃትን ያደረሰው የሶሪያ መንግሥት መሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ተገለጸ

በቅርቡ በሶሪያ የደረሰውን የኬሚካል ጥቃትን የፈጸመው  በሶሪያ የሚገኙ  አማጺያን ሳይሆኑ የሶሪያ  መንግሥት  መሆኑን  መረጃዎች  እየጠቆሙ  መሆኑ ተገለጸ ።

በሰሜን ሶሪያ ለሲቪሎች መገደልና መቁሰል ምክንያት ለሆነው የኬሚካል ጥቃት ተጠያቂዎቹ  የሶሪያ አማጺያን መሆናቸውን  ሩሲያ  ያቀረበችው ክስ ተቀባይነት እንደሌለው ተገልጿል ። 

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርና የሶሪያ አማጺያን አዛዥ ከጦር መሣሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን  በሠጡት  መግለጫ እንደገለጹት የኬሚካል ጥቃቱ የደረሰው በሶሪያ መንግሥት የጦር ኃይል መሆኑን መረጃዎች  አመላክተዋል ። 

የሶሪያ መንግሥት የኬሚካል ጥቃቱን በጦር ኃይሉ መፈጸሙን  ያሰተባባለ ሲሆን በሶሪያ ጉዳይ  ላይ በብራስልስ  ለማካሄደ  በታሰበው  ጉባኤ ላይ  ከወዲሁ  ተጽዕኖ እንዳያሰድር ተሰግቷል ።             

የተባበሩት  መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኬሚካል ጥቃቱ ላይ የሚመክር ጉባኤን  ለማካሄድ  ዝግጅቶችን  እያጠናቀቀ ይገኛል ።

መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገው  የሶሪያ የሰብዓዊ ቀውስ አጣሪ  ቡድን  በሰሜን  ሶሪያ በደረሰው  የኬሚካል  ጥቃት 80 ሰዎች መገደላቸውንና  20 የሚሆኑት ህጻናት እንደሆኑ አረጋግጧል ።