336 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

የካቲት 10/2013 (ዋልታ) – 336 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ ዜጎችን በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ በሪያድ – ሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ አስታውቋል።