ቱርክ ፓርላሜንታዊ ሥርዓቷን ወደ ፕሬዚዳንታዊ ለመቀየር የህዝበ ውሳኔ አስተላለፈች

ቱርክ ፓርላሜንታዊ ሥርዓቷን ወደ ፕሬዚዳንታዊ አስተዳደር ለመቀየር የሚያስችል ህዝበ ውሳኔ  አስተላላፈች ።

ቱርክ ከዚህ ቀደም ፓርላሜንታዊ የሆነ የመንግሥት አስተዳደርን ትከተል የነበረ ሲሆን አገሪቱን ወደ ዘመናዊ አስተዳደር የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ ነው የመንግሥት አስተዳደሩን ፕሬዚዳንታዊ ለማድረግ ህዝበ  ውሳኔ  ማካሄድ ያስፈለገው ።

በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዚደንት ሬሲፕ ኤርዶጋን የአገሪቱ ፓርላሜንታዊ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ፕሬዚዳንታዊ እንዲቀየር ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግበት ሓሳብ በማንጨት ተግባራዊ እንዲሆን ሚና ተጫውተዋል ።

የቱርክ መንግሥትን የሚቃወሙ ኃይሎች  በበኩላቸው በአገሪቱ  የመንግሥት የአስተዳደር  ሥርዓት ወደ ፕሬዚዳንታዊ መቀየሩ አምባገነንነትን ይበልጥ ያጠናክራል የሚል አስተያየታቸውን ይሠጣሉ ።

የፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት በአገሪቱ መስፈኑ የፕሬዚዳንቱን  የሥልጣን ዕድሜ ከማራዘም ያለፈ  ፋይዳ እንደሌለው ትችታቸውን ያቀርባሉ  ።              

 በቱርክ  የመንግሥታዊ አስተዳደር ሥርዓቱን መቀየር ያስፈልጋል አያስፈልግም የሚለው እሠጣ ገባ  እየቀጠለ በመጣበት  ወቅት  ህዝበ ውሳኔው እንዲካሄድ የተደረገ ሲሆን   በ167ሺህ በላይ ምርጫ መስጫ ጣቢያዎች ተዘጋጀተው 55 ሚሊዮን ህዝብ ተመዝግቦ ድምጽ መሥጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል ።

በህዝበ ውሳኔ ውጤቱም  መሠረት  ፓርላሜንታዊ ሥርዓቱ  በፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት ይተካ  የሚሉት  የፕሬዚዳንቱ  ደጋፊዎች በ 51  በመቶ  ድምጽን  በማግኘት አሸናፊ መሆን ችለዋል ።

ከህዝበ ውሳኔው ውጤት በኋላ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን ለቱርክ ህዝብ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የቱርክ ህዝብ ታሪካዊ ውሳኔ አስተላልፏል በማለት የተገኘውን ውጤት አድንቀዋል ።  

የቱርክ መንግሥት  ተቀዋሚ ፓርቲ  የሆነው የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ የምርጫው ውጤት እንደተጭበረበረ ቅሬታቸውን በመግለጽ የህዝቡ ድምጽ ድጋሚ እንዲቆጠር አሳስቧል ።

አንዳንድ አስተያያት ሰጪዎች  እንደሚገልጹት የደጋፊዎችና የተቃዋሚዎች የሠጡት ድምጽ  መቀራረብ   በምርጫው  ማጭበርበር እንደነበር ያመላክታል ይላሉ ።

በአንድ የምርጫ ጣቢያ ሶስት ሰዎች መሞታቸውም ምርጫው ችግር እንደነበረበት ማሳያ እንደሆነ አስተያያት ሰጪዎቹ ይጠቁማሉ ፡፡

 

ህዝበ ውሳኔውን  ተከትሎ ባለፈው ሳምንት  በቱርክ የተለያዩ ከተሞች አደባባዮች ተቀዋሚዎችንና ደጋፊዎችን በማስተናገድ  ሥራ እንደተጠመዱ ተመልክቷል  ፡፡

በቱርክ ተግባራዊ  እንዲደረግ የሚፈለገው ለፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት ፕሬዚደንቱ  ካቢኔ አፍርሶ የመገንባት፣ ፓርላማ እስከ መበተን የሚደርስ ስልጣንና የመሳሰሉ ኃላፊነቶችን የሚሠጥ ከመሆኑም ባሻገር   አሁንያሉት ፕሬዚዳንት እኤአ 2029 ድረስ በሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ዕድል ይፈጥራል

የኢትዮጵያን የቱሪዝም አቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ አምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር መመደቡን የቱሪዝም ድርጅቱ አስታውቋል።( ምንጭ  ቢቢሲ)