338 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

መጋቢት 10/2013 (ዋልታ) – 338 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በተለያዩ አገራት በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ሥራ እየሰራ ነው፡፡