የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በኒዩክለር መረሀ ግብር ዙሪያ ለመነጋገር ሰሜን ኮሪያ ገቡ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በኒዩክለር መረሀ ግብርና ለሶስት አመታት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በተደረገው ጦርነት የሞቱትን የአሜሪካን ወታደሮች ቅሪት ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ለመነጋገር ሰሜን ኮሪያ ገብተዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰሜን ኮሪያ የኒዩክለር መርህ ግብር ግንባታ በሚወገድበት ዝርዝርና በጦርነት ወቅት የሞቱ የአሜሪካ ወታደሮችን ቅሪት ለማስመለስ ከሰሜን ኮሪያ ባለስጣናት ለመነጋገር ፒዮንግያንግ ገብተዋል፡፡

ፖምፒዮ በፒዮንግያንግ በቀደሙት ግዚያት አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገር ምክኒያት የሆኑትን ኪምዮንግ ቾልን አንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

ኪምዮንግ ቾል ፕሬዝዳንት ትራምፕና ኪም ጆንግ ኡን በሲንጋፖር እንዲገነኙ ዋናኛውን ድርሻ የተወጡ ሲሆን ፖምፒዮ አስከ ነገ በሚኖራቸው ቆይታ ሰሜን ኮሪያ የኒዩክለር መርሀ ግብሯን ለማቋረጥ ያስተለለፈችውን ውሳኔ በተመለከተ ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆነች ጥልቅ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሲንጋፖር ባደረጉት ቆይታ ኪም ሀገራቸው የኒዩክለር ግንባታዎቿን ለማስወገድ ፍቃደኛ መሆኗን ቢገልፁም መቼና አንዴት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ዝርዝር ነገር ላይ አለመድረሳቸው አይዘነጋም፡፡  

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኮሪያ ከመድረሳቸው አስቀድሞ በስልክ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኪም ለኮሪያውያን መፃኢ እድል ሲሉ ዙሪያ ገብ አማራጮችን ከግምት ውስጥ አንደሚያስገቡ እምነት እንዳላቸው ገልፀውላቸዋል፡፡

ከሰሜን ኮሪያ መሪዎችም በመገናኘት ከሰላም ከሚገኘው ፍሬ ዙሪያ አበክሬ መክራለው ሲሉም ፖምፒዮ ለትራምፕ አሳውቀዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ ለአሜሪካም ሆነ ለአለም በገባቸው ቃል መሰረት መርሀ ግብሯን አስመልክቶ በቀጥታ ወደ ተግባር ስለመግባቷ ቢያንስ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች በተያያዘ ለልእለ ሀያሏ ደህንነት ሀይሎች ግልፅ እንድታደርግ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሌላው አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ባደረገቸው የሶስት አመት ጦርነት ማለትም ከፈረንጆቹ 1950 አስከ 1953 ዘመቻ የጠፉባትን ወታደሮች ፍንጭ አስመልክቶ ምክክር እንደሚያደረጉ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በሁለቱ ነጥቦች የሚደረገው ውይይት ኪም በሲንጋፖር በገቡት ቃል መሰረት ስለመገኘታቸው የሚያመላክት ከመሆኑም በላይ በቀጣይ ውጤት ካልታየበት ከዋሺንግተን በኩል ጥብቅ ማዕቀብ ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ ስጋት አሳድሯል፡፡

ዋስንግተን ሰሜን ኮሪያ የ200 ወታደሪቿን ቅሪት እንዲመለስላት በጥብቅ የምትሻ ሲሆን የሞቱ ወታደሮችን ቅሪት በምርመራ የመለየት ስራውን ለማከነውን በሚረዳት ጉዳይ ዙሪያ ፖምፒዮ ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (ሮይተርስ)