ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ መሪዎች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ መሪዎች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

የአዉሮፓ ህበረት ላለፉት ሁለት ዓመታት የአሜሪካ ከፍተኛ የገበያ መዳረሻ እንደነበር ይነገርለታል፡፡

በዚህም አሜሪካ ከህብረቱ በዓመት እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች፡፡ አሜሪካ ደግሞ ለውትድርናው ዘርፍ ከፍተኛ በጀት ከሚመድቡ የዓለም ሀገራት መካከል በአንደኝነት ትጠቀሳለች፡፡

ምንም እንኳ የአዉሮፓው ህብረት የኔቶን ዓመታዊ በጀት ዩ.ኤስ 15 ከመቶውን ትሸፍናች ብልም  የተቋሙ 22 በመቶ ዓመታዊ በጀት የሚይዘው ከአሜሪካ  መንግስት የሚበጀተው በጀት መሆኑን የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር እየገለጸ ይገኛል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገና ወደ መምበረ ስልጣናቸው ሲመጡ ስለ ኔቶ ሲናገሩ ኔቶ ጊዜ ያለፈበት ያረጀ ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡ እናም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ለኔቶ የምትመድበው አመታዊ በጀት 22 በመቶም ይሁን 15 በመቶ ከዚህ መውረድ አለበት ባይ ናቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኔቶ አባል ሀገራት ቁጥር ከ29 መብለጥ የለበትም ባይ ናቸው፡፡ እንዳውም በ1949 እንደ ነበረው 12 ብቻ መሆን አለበት ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሞግታሉ፡፡

በዚሁ ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኔቶ አበል ሀገራት መሪዎች ጋር በብራሰልስ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ታዲያ በሁለቱ መሪዎች መካከል የሚኖረው ንግግር ሰላም ያለው እንዳልሆነ እየተነገረለት ነው፡፡ ይህንንም በማሰብ ዶናልድ ጄ ትራምፕ ለኔቶ ያለዉን አመለካከት ካሁኑ እንዲያስተካክሉ የአዉሮፓው ህብረት መልክት እየላከላቸው ይገኛል ነው የተባለው፡፡

የአዉሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ታስክ ለሚስተር ትራምፕ በላኩት መልዕክት አሜሪካ ከአዉሮፓ በላይ ተባባሪ እንደለላት ገልጸዋል፡፡

በተለይም የመስከረም 9ኙ ጥቃትን በማስመልከት የአሜሪካ እና የኔቶ ወታደሮች በጋራ በአፍጋኒስታን የከፈሉትን ዋጋ በማስታወስ፡፡ ለኔቶ አነስትኛ በጀት ይመድባሉ ተብለው በህበረቱ ከተፈረጁት ሀገራት መካከል ሩሲያ አንዷ ስትሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሀሳብ የሚስማሙ መስለዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቀጣይ ቀጠሯቸው የሚሆነው ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መወያየት እና ሀገራቸው ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማስተካከል ነውም ተብሏል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ይመስላል አሜሪካ ከአዉሮፓ በላይ ወዳጅ የላትም በማለት ፕሬዝዳንቱን ለማግባባት ጥረት እያደረጉ የሚገኙት፡፡ ዶናልድ ታስክ ሩሲያ ለኔቶ ከምትመድበው ዓመታዊ በጀት የአዉሮፓው ህብረት ከሚመድበው በእጅጉ አነስተኛ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንት ዶናለድ ትራምፕ በርካታ የኔቶ አባል ሀገራት የአውሮፓ ሀገራት በመሆናቸው ከፍተኛውን የኔቶን በጀት መሸፈን አለባቸው፡፡ ይሁንና ከአዉሮፓ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላቸው እንግሊዝ፣ ግሪክ እና ኢስቶኒያ 2 በመቶ በጀቱን ብቻ ነው የሚችሉት፡፡ ይህ ደግሞ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናለድ ትራምፕ የኢፍትህሃዊነት ጥያቄን የሚያስነሳ ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በብረት እና በአሉሚኒየም ላይ የጣሉት ታሪፍ እንዳለ ሆኖ አሁን ደግሞ በኔቶ ጉዳይ መምጣታቸው ህብረቱን በእጅጉ አስጨንቆታል፡፡  

በእንዲህም አይነት ሁኔታ ወዳጅነታችን ቀጣይነት ሊኖረው አይችልም ብለዋል የጀርመኗ መርህተ መንግስት አንጌላ ሜርክል፡፡ ይህም ወደጅነታቸውን እንደማይፈታተን ፕሬዝዳንት ትራምፕ መናገራቸዉን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡