ኢራን በአሜሪካ ላይ የምታሰማውን ዛቻ ካላቆመች አፀፋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል አሜሪካ አስጠነቀቀች

ኢራን በአሜሪካ ላይ የምታሰማውን ዛቻ ካላቆመች አፀፋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል አሜሪካ አስጠነቀቀች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የአሜሪካ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳላስገረመው  ገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በሳምንቱ መጨረሻ በትዊተር ገጻቸው ሁለቱ አገራትን የሚመለከተውን ሥራቸውን ለመሥራት ጊዜ አልፈጀባቸውም። የተለመዱ የነቆራና አወዛጋቢ ሓሳቦችን በቲዊተራቸው ፅፈዋል።  

የ2015ቱን የኢራን የኒዉክለር ስምምነት መና ያስቀሩት የአሜሪካ መሪ ኢራን ለአረቡም ዓለም ሆነ ለእስራኤል ስጋት ናት ብለው ያምናሉ፡፡

ከኢራን  ጋር  ያለው  ሁኔታ ከመልካሙ ይልቅ ከአሉታዊ ነገር ጋር ተያያዥ እንደሆነ የሚነገርላቸው ፕሬዝዳንት ትረምፕ ወደ መንበረ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የአሜሪካ ስጋት አድርገዉ  ከሚቆጥሯቸው አገራት ውስጥ ኢራን አንዷ ነች።

ኢራን የምትታማበት የኒኩለር ማበልፀግ ተግባሯ የፕሬዝደንት ትራምፕን ትኩረት የሆነውም ለዚሁ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ኢራን በተለይም የኒኩሊየር ማበልፀግ ህልሟ እዉን ሆኖ መሣሪያዉን ከመዳፏ ያስገባች እለት ደግሞ ምዕራባዊያኑ በተለይም አሜሪካ ቀዳሚዋ የመሳሪያ መሞከሪያ ምድር ትሆናለች የሚለዉ ስጋት ፕሬዝደንት ትራምፕን እንቅልፍ ሳይነሳም አልቀረም።

በመካከለኛዉ ምስራቅ የፖለቲካ የበላይነት ለማግኘት በሚደረገዉ እሽቅድምድም ውስጥ የኢራን ወቅታዊ አቋም አስፈሪ መሆኑን ተከትሎ ሀገሪቷ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁጥር አንድ ወዳጅ ከሆነችው እስራኤል ጋር የምታደርገዉ ንትርክም ለፕሬዝዳንቱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል፡፡

ታዲያ ይህ የሁለቱ ሀገራት ባላንጣነት እንዳለ ሆኖ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአገሪቱ  እኤአ በ2015 በዘመነ ኦባማ ከፈረመችው የኢራን የኒኩለር ስምምነት ሀገራቸዉን ማስወጣታቸዉ  በቋፍ ላይ ያለዉን የሀገራቱን ግንኙነቱ አባብሶታል ።

ክስተቱን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የቃላት ጦርነት እያየለ መጥቷል፡፡ ሀገራቱ ሲወራወሯቸዉ የቆዩት ስድብ አዘል ቃላት ሀገራቱን ወደ ለየለት ግጭት እንዳያስገባም ተሰግቷል።

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራመፕ ከኒዉ ጀርሲዉ ጉዟቸዉ መልስ በቲዊተር ገጻቸው ላይ ለኢራን ያስተላለፉት መልዕክት ጠንከር ያሉ የማስጠንቀቂ ነው።

“ከዚህ በኋላ ዳግም አሜሪካን ለማስፈራራት እንዳታስቡ፤ ያ ከሆነ ግን በአፀፋዉ ዓለም በታሪክ አይቶት የማታቀዉ አስከፊ ታሪክ በናንተ ላይ ይሆናል።” ብለዋል ፕሬዝዳንት ትረምፕ፡

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖፒዮ ኢራን ከነዳጅ ሽያጭ የምታገኘውን ሀገራቸው በወራት ውስጥ ዜሮ ለማድረግ እየስራች እንዳለ አስታወቀዋል፡፡