የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በማይናማር የደረሰውን ሰብዓዊ በደል የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቋመ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማይናማር የደረሰውን ሰብአዊ በደል የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቁሟል።  

ኮሚቴው በማይናማር ሙስሊም ላይ የደረሰዉን አሰቃቂና ኢ ሰብአዊ ወንጀልን በተመለከተ መረጃዎችን የማሰባሰብና የማራጀት ስራዎችን ይሰራል ተብሏል።

ቻይና፣ ፊሊፒንስ እና ቡሩንዲ ኮሜቴ የማቋቋሙን ውሳኔው የተቃወሙ ሀገራጽ መሆናቸው ታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ም/ቤት እንዳስታወቀዉ በማይናማር ሙስሊም ላይ የደረሰዉን አሰቃቂ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ መረጃዎችን የሚያሰባስብና የሚያደራጅ ኮሚቴ አቋቁሟል።

ኮሚቴዉ ይፋ የሚያደርገዉን መረጃ ተከትሎም በሮሂንጋዎች ላይ በደል የፈፀሙ አካላት ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

በአዉሮፓ ህብረት እና በስላማዊ ትብብር ድርጀት አነሳሽነት የቀረበዉ የማይናማር በደል የሚያጣራ ኮሚቴን የማቋቋም የዉሳኔ ሀሳብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ምክክር ከተደረገበት በኋላ ከ47ቱ የምክር ቤቱ አባላት ሀገራት የ35ቱን ይሁንታ አግኝቶ ከሚተው ባሳለፍነው ሀሙስ ተቋቁሟል።

ቻይና፣ ፊሊፒንስ እና አፍሪካዊቷ ቡሩንዲ ውሳኔውን የተቃወሙ ሀገራ ናቸዉ ተብሏል። በነጋራችን ላይ የቀድመዋ በርማ ያሆኗ ማይናማር በእስያ አህጉር የምትገኝ ሀገር ስትሆን አብዛናው ህዝቧ የቡድሃ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ የማይናማር ሙስሊሞች ቸሮሂንጋ ይባላሉ፡፡

ከአመት በፊት የአራካን ሙስሊሞች ነፃ አዉጪ ጦር በምያንማር መንግስት የፖሊስ እና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት በአፀፋዉ እጅግ አሰቃቂና ሰብዓዊነት የጎደለው እንምጃን በሮሂንጋዎች ላይ ወስዷል፡፡

 በማይናማር የዜግነት ክብር ተነፍጓቸዉ ለአመታት በባይተዋርነት ሲታዩ የቆዩት ሮሂንጋዎች ለአመታት የኖሩበት የመገለል ህይወት አልበቃ ብሏቸዉ አሰቃቂዉ ጭፍጨፋ ተጨምሮበታል፡፡

 የመንግስት ወታደሮች እና የሂንዱ እምነት ተከታዮች የሚያርሱባቸውን ክፉ በትር ለመሸሽ ጓዜን ማቄን ሳይሉ የማይናማር ሮዊጋዎች ወደ አጎራባች ሀገራት ለመሰደድ ተደገዋል። ራንኪ የሚባለው በብኣት የሚኖሩበት አካባቢም ብታቸው ወድሟል፡፡

ሁለታው አሳስቧቸው ከመኖሪያ ቄያቸው ያመለጡ 7 መቶ ሺ ሮሂንጋዎች ደግሞ ዛሬም ድረስ የሰቆቃ ህይወትን በጎረቤት ባንግላዲሽ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁኔታው ለዓለም አቀፉ ማህበረስብ ያሳወቁት የሮይትስ ጋዜጠኞችም ከመታሰር አልዳኑም፡፡ 

በርግጥ አሁን የተሰማው ዜና በህይወት የተለዩዋቸዉን ወገኖቻቸዉን ባይመልስላቸዉም ጥፋተኞችን ለፍርድ በማቅረብ የሮጊንጋዊያንን እንባ ያብሳል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲስ የተቋቋመው መርማሪ ኮሚቴ ከ2017ቱ የግፍ ተግባር በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በሮሂንጋዊያን ላይ ሲደርስ የነበረውን በደል ሁሉ በመመርመር በወንጀለኞች ላይ ለሚከፈተዉ የክስ መዝገብ ተጨባጭ ሰነዶችን በማደራጀት የሚያቀርብ ይሆናልም ተብሏል።

በተጨማሪም ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በቀጣይ ለሚያካሂደው የወንጀል ምርመራ አዲስ የተቋቋመው አካል መረጃዎችን በማቅረብ አብሮት ይሰራልም ነዉ የተባለዉ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማይናማር አምባሳደር ክያዉ ሞ ቱን እንደሚሉት ግን ዉሳኔዉ የተባሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ አጣሪ ተልዕኮ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተመስርቶ የተወሰነ እና መንግስታቸውን ከዚህ ቀደም ዉድቅ ያደረገዉ በመሆኑ ተቀባይነት አይኖረዉም ብለዋል።

 ዉሳኔዉ ፍትሀዊነት የሌለዉ ከመሆኑም ባለፈ ለአንድ ወገን ያደላና የሀገሪቱን አንድነት የሚሸረሽር ነዉ ሲሉም አምባሳደር ሞ ቱን ተቃውሞዋቸውን አስምተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በሮሂንጋዎች ላይ ለደረሰዉ በደል ተጨባጭ መረጃዎች እንዳሉት እና በርግጥም የሀገሪቱ ጦር በርካታ ንፁሀንን እንደገደለ ገልጿል፡፡ ለዚህም የሀገሪቱን የጦር አዛዥ ሚን አን ህላኢንግን ጨምሮ አምስት ጀነራሎች ለሰሩት በደል ፍርድ መቀበል አለባቸዉ የሚል የፀና አቋም ይዟል።

የቻይና መንግስትም በአንፃሩ የተቋቋመዉ ኮሚቴ በሀገሪቱ ያለዉን ዉጥረት ያባብሳል በሚል ስጋት ዉሳኔዉን መቃወሙ ተነግሯል።

በተያያዘ ዜና የካናዳ መንግስት የማይንማር መሪ የሆኑት የቀድሞዋ የሰላም ኖቤል አሸናፊ አን ሳን ሱ ኪ ከሀገሪቱ መንግስት ተችሯት የነበረዉ የክብር ዜግነት እንዲነሳ ዉሳኔ አስተላልፏል።

የካናዳ መንግስት ውሳኔዉ ላይ የደረሰዉ አን ሳን ሱ ኪ ከአመት በፊት በማይናማር የተካሄደዉን ጭፍጨፋ ማቆም ባለመቻላቸዉ ነዉ ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።

የተባበሩት መንግስታት ደርጅት የማይናመር ሙስሊሞች ላይ የተካሄደውን ኢሰባአው ደርጊት ለዓለም ማህበረሰብ በማጋለጣቸው የታስሩት ጋዜጠኖችም እንደለቀቁ የማይናመር መንግስት ጠይቋል፡፡