የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ (ትልቁ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለጸ ።
ትልቁ ጆርጅ ቡሽ በመባል የሚታወቁት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በ94 ዓመታቸው ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ልጃቸው ገልጸዋል ።
ጆርጅ ቡሽ 41ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ እኤአ ከ1989 እስከ 1993 በፕሬዚደንትነት ፣ ሁለት ተርም ደግሞ የፕሬዚደንት ሬገን ምክትል በመሆን አገልግለዋል ።
ትቅሉ ጆርጅ ቡሽ ባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ ሆስፒታል በመግባት የደም ኢንፌክሽን በሽታን ለመከላከል ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው እንደነበር ተገልጿል ።
ልጃቸው ጆርጅ ቡሽ የአባታቸውን ሞት አስመልክተው በሠጡት መግለጫ አባታችን በህይወት ከኛ በመለየታቸው እጅጉን አንዘናል ብለዋል ።
ትልቁ ጆርጅ ቡሽ የትልቅ ስብዕና ትልቅ አባት እንዲሁም ለአገራቸው ታለቅ ዋጋ የከፈሉ መሆናቸውን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የጆርጅ ቡሽን ሞት አስመልክተው ለሪፐብሊካን በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል ።
ጆርጅ ቡሽ እኤአ በ1964 ወደ አሜሪካ ፖለቲካ የተቀላቀሉ ሲሆን በ40 ዓመታቸው የቴክሳስ የነዳጅ ንግድ ተቋም በመመሥረት ሚሊየነር መሆን ችለው ነበር ።
በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ጆርጅ ቡሽ በጦር አውሮፕላን አብራሪ በመሆን አሜሪካ በጃፓንን ላይ በከፈተችው በቦንብ ድብደባ ዘመቻ የተሳተፉና እኤአ በ1944 አውሮፕላናቸው በጃፓኖች ተመቶ በህይወት መትረፋቸውን የታሪክ ድርሳናት ጠቁመዋል ።
ትልቁ ጆርጅ ቡሽ አምስት ልጆችና 17 የልጅ ልጆችን ፣ ስምንት የልጅ ፣ ልጅ ልጅ ማየት የቻሉና ትልቀ ቤተሰብ መመሥረት የቻሉ ናቸው ።