አሜሪካ እና ሩሲያ የቬንዙዌላን ቀውስ ለማብረድ በሮም እየመከሩ ነው

አሜሪካ እና ሩሲያ በቬንዙዌላ የተከሰተው ቀውስ ለማብረድ እና የፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማድሮ አገዛዝን ህጋዊ ለማድረግ በጣሊያን ሮም እየተወያዩ ነው፡፡

ከወራት በፊት በቬንዙዌላ የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማድሮ ማሸነፋቸውን ቢያውጁም ተቃዋሚያቸው ዩዋን ጓይዶ  ግን ምርጫው ተጭበርብሯል አሸናፊው እኔ ነኝ በማለት በሀገሪቱ እስካሁንም የማያባራ ቀውስ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህ ቀውስ አሜሪካ ተቃዋሚው ዩዋን ጓይዶን በአንፃሩ ደግሞ ሩሲያ የማድሮን መንግስትን ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡የአለምን ፖለቲካ የሚዘውሩት ሁለቱ ሀያላን ሀገራት በቬንዙዌላ አላባራ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ለማብረድ ከፍተኛ አመራሮቻቸው በጠረጰዛ ዙሪያ በሮም እየተወያዩ ነው፡፡

ሩሲያ ኒኮላስ ማድሮ የሀገሪቱ ብቸኛው ህጋዊ  ፕሬዝዳንት ነው ብላ የምታምን ሲሆን አሜሪካ እና በርካታ ምዕራባዊያን ሀገራት ደግሞ ፊታቸውን ወደ ተቃዋሚው ዩዋን ጓይዶ አዙረዋል፡፡

የሀገሪቱ ዜጎች ከዚህ የፖለቲካ ንትርክ እንዲወጡ እና የሰላም አየርን እንዲተነፍሱ ለማድረግ ይመስላል አሜሪካ እና ሩሲያ በቬንዙዌላ ጉዳይ ለውይይት የተቀመጡት፡፡

በአሜሪካ በኩል ለዚህ ውይይት የተቀመጡት ኢሊዮት አብራም በቬንዙዌላ ጉዳይ ላይ የተደረገው ውይይት መልካም እና መግባባት ላይ የምንደርስበት ይሆናል ሲሉ የገለፁ ሲሆን በሩሲያ በኩል ለውይይት የተቀመጡት የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ራይብኮቭ ውይይቱ በቬንዙዌላ ሰላምን ለማስፈን የሚረዳ ሲሆን ዋሽንግተን ግን ያስቀመጥናቸውን አቋሞችና ማስጠንቀቂያዎች ልታከብር ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሰርጌ ራይብኮቭ ለሩሲያው የዜና ወኪል  እንደገለፁት ውይይቱ ትንሽ አስቸጋሪ ቢሆንም ነገር ግን ሞስኮ ዋሽንግተን በቬንዙዌላ ወታደራዊ ጣልቃገብነቷን እንድታቆም ጠይቃለች ነው ያሉት፡፡

የአሜሪካው ተወካይ ዲፕሎማት  አብራምስ በበኩላቸው በቬንዙዌላ የፕሬዝዳንት ስያሜን ማን ያግገኝ የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚቀመጥ ነው ብለዋል፡፡ነገር ግን በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የቬንዙዌላ ቀውስ እንዴት ይቁም የሚለውን ቅድሚያ ሰጥተው ተወያይተውበታል ነው ያሉት፡፡

ሩሲያም በቬንዙዌላ ላይ ከአሜሪካና ላቲን አሜሪካ ሀገራት የተጣለባትን ማዕቀብ ትኩረት አድርጋ ተወያይታበታለች፡፡በነዳጅ ምርት ሽያጭ ላይ ኢኮኖሚዋ የተመረኮዘዘው  ቬንዙዌላ ከአሜሪካ በተጣለባት ማዕቀብ የተነሳ በወር ከ50ሺህ በላይ በርሚል ነዳጅ ኪሳራ እደረሰሰባት ይገኛል፡፡

ይሄ ደግሞ ለቬንዙዌላ እንደ ውድቀት የሚቆጠር ነው ሲሆን ችግሩነ  ለመፍታት መፍትሄዎች ጠረጴዛ ላይ ናቸው ይላሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፡፡

ሩሲያ የማድሮን መንግስትን ስትደግፍ የቆች ሲሆን አሜሪካ ደግሞ የተቃዋሚ ሀይል መሪውን ዩዋን ጓይዶ ስትደግፍ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡