የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት በሙስና ተጠርጥረው ታሠሩ

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሚሼል ቴመር በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው ተገለጸ፡፡

ሪዮ ዴጄኒሮ ፖሊስ ቢሮ በ1ዐ ግለሠቦች ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣ ሲሆን ከእነዚህም አንዱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሚሼል ቴመር ናቸው፡፡

በሌሎች 26 ተጠርጣሪዎች ላይም ሌላ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ቴመር ግን የአሁኑን ጨምሮ በተደጋጋሚ የሚቀርብባቸው ሙስናዊ ክስ ሲያጣጥሉ ቆይተዋል፡፡

በዚህ ካርውሽ በተባለው ዘመቻ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞችና የትግል ተቋማት መሪዎች ናቸው እየታሠሩ የሚገኙት፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)