ኢራንና ፓኪስታን የሽብር ጥቃትን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

ኢራን እና ፓኪስታን በጋራ ድንበሮቻቸው አካባቢ የሽብር ጥቃትን ለመከላከል ተስማሙ፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ በትላንትናው እለት እንዳስታወቁት ለይፋዊ ጉብኝት ቴህራን ከገቡት አዲሱ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን በድንበሮቻቸው አካባቢ የሚቃጣውን የሽብር ፅቃት ለማስቆም መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሰፈነውን ውጥረት ተከትሎ ቴህራን እና ኢስላማባድ ጉዳዩን ለማርገብ በጠረጰዛ ዙሪያ ተስማምተዋል ሲሉ ሩሀኒ አክለዋል፡፡

በስፋት ድንገተኛ የሽብር ጥቃት ከሚደርስባቸው አካባቢዎች የኢራቋ ደቡብ ምስራቃዊ ሲስታን ባሉቺስታን ትጠቀሳለች፡፡ በባለፈው የፈረንጆቹ አመት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት የፓኪስታኑ መሪ ኢምራን ካህን ኢራንን ጎብኝተዋል፡፡

መሪዎቹ በባለፈው ሳምንት በሀገራቱ ድንበር አካባቢ 14 የፓኪስታን ወታደሮች መሞታቸውን ተከትሎ ኢስላማባድ ጉዳዩ እንዲጣራ በጥብቅ ትሻለች፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም የፀጥታ አካላት ከሁለቱም በኩል ተወክለው የመከሩ ሲሆን፣ ከስምምነት ላይ የደረሱባቸው ነጥቦች ይፋ አለመሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ከቴህራንም ሆነ ከኢስላማባድ በየትኛውም በኩል ጥቃቶችን ለመከላከል እና  ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ በኩል ሁለቱም ሀገራት በመተማመን ይስራሉ ሲሉ ኢምራን ካሀን አስታውቀዋል፡፡

የኢራኑ መሪ ሀሰን ሩሀኒ አስቀድሞ 27 አብዮት ጠባቂዎች ተገለውብኛል በሚል ምክንያት ፓኪስታን በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ እንድታቀርብ ፍላጎት ስታሳይ ቆይታለች፤ አሁን ግን በመተማማን ላይ የተመሰረተ ተግባር ለመፈፀም ፍቀደኛ ነን ሲሉ አስረድተዋል፡

በተጠቀሰው ጥቃት ኢራን በሱሲ ጂሀዲስት አጥፍቶ ጠፊ ደርሶብኛል የሚል ክስ ስታቀርብ ብትቆይም ቴህራን ከእውቅናዬም ከድንበሬም የራቀ ጉዳይ ነው ስትል ቆይታለች፡፡

የጥቃቱ አድራሾች ስልጠናም መሳሪያም ከኢራን በኩል ስደገፉ እንደነበረ ማረጋገጫ በእጄ ገብቷልም ትላለች ቴህራን፡፡

አሁን በደረሱበት ስምምነት ግን ሌላ ሶስተኛ ጣልቃ የሚገባ ሀገር ሳይኖር ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መወሰናቸውን እና በአሜሪካ የሚቃጣውን የስላማዊ ሪፐብሊክ ሀገራትን የማግለል ሴራ እንደሚያቆሙት ሩሀኒ በንግግራቸው አረጋግጠዋል፡፡

በቴህራንና በኢስላማባድ መካከል የሚደረገው የንግድ ልውውጥም እንደሚጠናከርና ኢራን የፓኪስታንን የነዳጅ ፍላጎት ለሟሟላት ዝግጁ መሆኗን የተናገሩ ሲሆን የኤሌክትሪክ ሀይል ለቴህራን ለመሸጥ ማቀዳቸውን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

የኢራን ካባር እና የፓኪስታን ዋዳር አየር መረፊያዎች በረራዎች እንደሚጠናከርና ቴህራንን ከኢስላማባድ የሚያስተሳስር የባቡር ፕሮጀክት እንደሚገነባም ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ አስታውቀዋል፡፡

ለጉብኝት በቴህራን የተገኙት ኢምራን ካሀንም በበኩላቸው ትብብሩ በሀይል አቅርቦትና መሰል ጉዳዮች እየተጠናከረ እንደሚሄድ ገልጸዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡