የሩሲያና የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንቶች ባደረጉት ውይይት ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሩሲያ ባደረጉት ውይይት ግንኙነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተስማምተዋል፡፡

ኪም በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ በደረሱበት ወቅት የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የመሪዎቹ ውይይት በኒዩክሌር ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩር ሩሲያ ገልጻ የነበረ ሲሆን ኪም በበኩላቸው አሜሪካ ውድቅ ባደረገችው የውይይት ጉዳይ ላይ ድጋፍ እንደሚጠብቁም ገልጸዋል፡፡

መሪዎቹ በመክፈቻ ንግግራቸው ሁለቱ አገራት የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ለሰሜን ኮሪያ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ አገራት የነበራቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በባቡር መሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎችም ዘርፎች ለማጠናከርም ተስማምተዋል፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)