የጃፓኑ ንጉስ አክሂቶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ሊለቁ ነው

በጃፓን ላለፉት 30 ዓመታት ንጉስ ሆነው ያገለገሉት የ85 ዓመት ንጉስ አክሂቶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተስማምተዋል፡፡

ንጉሱ ከ200 ዓመታት ወዲህ በፍላጎት ስልጣን ለመልቀት የተስማሙት የመጀመሪያ ንጉስ ናቸው ተብሏል፡፡

ንጉሱ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የተስማሙት እድሜቸው እየገፋ በመሄዱና የጤናቸው ሁኔታ ስራቸውን መስራት አስቸጋሪ በማድረጉ ነው የተባለው፡፡

የንጉሱ ስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ በአገሪቱ ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በዛሬው እለት የስልጣን ርክክብ ሂደት ተጀምሯል፡፡

ንጉስ በአገሪቱ ምንም የፖለቲካ ስልጣን ሚና ባይኖረውም ለጃፓን እንደ ብሄራዊ አርማ ተደርጎ ይወሰዳል ነው የተባለው፡፡

ንጉስ አክሂቶ በልጃቸው ናሩሂቶ የሚተኩ ሲሆን፣ ናሩሂቶ ከነገ ጀምረው የጃፓን ንጉስ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

(ምንጭ፡- ቢቢሲ)