ኢራን ኒውክለር የማበልፀግ መርሃ ግብሯን እንደምትቀጥል ገለጸች

ኢራን ያቋረጠችዉን የኒውክለር ማበልጸግ መርሃ ግብር ልትቀጥል እንደምትችል የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሃኒ አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያስታወቁት የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ዛሬ ወደ ኢራቅ ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ አሜሪካ በባህረ ሰላጤው አካባቢ የጦር አውሮፕላኖች ተሸካሚ መርከቦችን ማሰማራቷን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡

እስካሁን በሀገር ውስጥ የተመረቱ የዩራኒየም ንጥረ ነገርን ወደ ሌሎች ሀገራት ከመላክ እንደምትቆጠብም አሳስበዋል፡፡

በሚቀጥሉት ስልሳ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለውን ዩራኒየም በሀገር ዉስጥ እንደምታመርትም አስጠንቅዋል ፕሬዝዳንቱ ሀሰን ሮሃኒ፡፡

ኢራን እአአ በ2015 የፈረመችውን አለም አቀፍ የኒውክለር ስምምነት አሜሪካ በቅርቡ ራሷን ማግለሏን ተከትሎ በተጣለባት ማዕቀብ ኢኮኖሚያዋ ለከፋ ጉዳት መጋለጡ ነው የተነገረው፡፡

ይህን ተከትሎ ኢራን ያቋረጠችውን የኒውክለር ማበልፀግ መርሃ ግብር እቀጥላለው ስትል
ከስምምነት ለደረሱ አገራት፡ ለፈረንሳይ፣ ለጀርመን፣ ለሩሲያ፣ ለቻይና እና ለእንግሊዝ ማሳወቋን ይፋ አድጋርለች፡፡

(ምንጭ፡-ቢቢሲ)