ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ጋር እንደሚወያዩ አስታወቁ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂን ፒንግ ጋር እንደሚወያዩ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ በቀጣይ ወር ጃፓን በሚካሄደው የቡድን 20 አባል ሃገራት ስብሰባ ላይ ከጂንፒንግ ጋር እንደሚወያዩ ነው ነው ያስታወቁት፡፡

በጃፓን አደርገዋለሁ ያሉት የሁለትዮሽ ውይይት ምናልባትም ውጤታማና አስደሳች ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የትራምፕ የእንወያያለን መግለጫ ሁለቱ ሃገራት የገቡት የንግድ ፍጥጫ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት የተሰጠ ነው።

አሜሪካ 200 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባላቸው የቻይና ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥን የጣለች ሲሆን፣ ቻይና በአንጻሩ 60 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባላቸው የአሜሪካ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ለመጣል መዘጋጀቷን አስታውቃለች።

ዋሽንግተን በበኩሏ በቀጣይ ወር 300 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ባላቸው የቻይና ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ለመጣል ስለማሰቧም ተነግሯል፡፡

( ምንጭ፡- ሪውተርስ)