በህንድ ምርጫ ናሬንዲራ ሞዲ አሸነፉ

በህንድ በተካሄደ ምርጫ ናሬንዲራ ሞዲ ህንድን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለመምራት ማሸነፋቸውን ማወቅ ተችሏል።
በገዥው ባሂራቲያ ጄናታ ፓርቲ የሚመራው ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ጥምረት 345 መቀመጫዎችን በማግኘትም እየመራ ነው።
ፓርቲው አሊያም ጥምረቱ ሀገር ለመምራት በታችኛው ምክር ቤት ካሉት 543 መቀመጫዎች በትንሹ 272 መቀመጫዎችን መያዝ የሚጠበቅበት ሲሆን አብላጫውን አግኝቷል።
ሞዲ በአውሮፓውያኑ 2014 አብዛኛውን ድምፅ ያገኙ ሲሆን አሁን ላያሸንፉ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ ነበር። 
ሞዲ ምንም እንኳን አገሪቷን በመሩበት ወቅት በተለያዩ ጉዳዮች ተቃውሞ ሲቀርብባቸው ቢቆዩም ድላቸውን እውን አድረገውታል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ጀቪር ሸርጊል ለቢቢሲ እንደተናገሩት "ውጤቱ በጣም አስደንጋጭ ነው" ብለዋል።
በምርጫውን እንሸነፋለን ብለው እንዳልጠበቁ የተናገሩት ቃል አቀባዩ በምርጫ ቅስቃሳችን ጥሩ እንዳልነበሩ አምነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ብለው በትዊተር ገፃቸው ላይ "ሕንድ በድጋሚ አሸነፈች" ሲሉ ያስታወቁ ሲሆን ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።