ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሂዋዌ የንግድ ስምምነት አካል ሊሆን እንደሚገባው ገለጹ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሂዋዌ የአሜሪካ እና ቻይና የንግድ ስምምነት አካል ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የቻይና እና አሜሪካ የንግድ ጦርነት ባለፉት ሳምንታት ተባብሶ ቀጥሎ የቀረጥ ጭማሪና የቃል ማስፈራርያ ሂደቶች ተስተናግዷል፡፡

አሜሪካ ሂዋዌ ብሄራዊ ደህንነቷ ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ስትከራከር ቤጂንግ በበኩሏ የካምፖኒውን ስም አጠፋሽ በማለት ስትወቅስ ቆይታለች፡፡

ዋሽንግተን ሂዋዌን በጥቁር መዝገብ ላይ በማስቀመጥ ኩባንያው ላይ ትኩረት አድርጋለች። 
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት በነጩ ቤተ መንግስት ለጋዜጠኞች እንዳሉት” ሁዋዌ የሆነ አደገኛ ነገር ነው፤ ከደኅንነትና ወታደራዊ አቋም አንፃር ምን እንዳደረጉ አይታቹሃል በጣም አደገኛ ነው”፡፡ 
የትራምፕ አስተዳደር ሂዋዌ የአለም ሁለተኛው ትለቁ ስማርት የስልክ ቀፎዎች አምራች ካምፓኒያ እንደሆነ በመግለፅ፤ ኩባንያው ከመንግስት ፈቃድ ሳያገኝ ከአሜሪካ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዳያደርግ ክልከላ ይደረገበታል ብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኩባንያው ከቢጂንግ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም የንግድ ስምምነት አካል ሊሆን እንደሚገባ መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።