ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከኃላፊነታቸው ሊለቁ ነው

የብርታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት የተከተሉትን መርህ ተከትሎ በተፈጠረባቸው ጫና ከስልጣናቸው ለመልቀቅ ተገደዋል ነው የተባለው፡፡

“እንደ ሀገር የቻልኩትን አድርጌያለሁ አሁን ግን ለሀገር ጥቅም ሲባል ቦታውን ለሌሎች መልቀቅ ይኖርብኛል ብለዋል” ጠቅላይ ሚኒስትሯ በስንብት ንግግራቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከፓርቲያቸው መሪነት እና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት መልቀቃቸውን ይፋ ያድርጉ እንጂ ተተኪያቸው እስኪመጣ ለመጪዎቹ 13 ቀናት ወይም እስከ ግንቦት 30 ድረስ በኃላፊነታቸው ይሰራሉ ተብሏል፡፡

ቴሬሳ ሜይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በምርጫ ከተሸነፉ በኃላ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡

(ምንጭ፡-ቢቢሲ)