የሆንግ ኮንግ ዋና አስተዳዳሪ ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ

የሆንግ ኮንግ ተጠርጣሪዎች ለቻይና ተላልፈው እንዲሰጡ የሚያደርገውን የህግ ማሻሻያ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውመዋል።

ይህን ተከትሎ የከፊል ራስ ገዟ ከተማ ሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ ቻሪየ ላም “የህዝቡን ሀሳብና ተቃውሞ በጉልህና በግልፅ ሰምተናል፤ በትህትና ይቅርታ እንጠይቃለን” ብለዋል።

ማንኛውም ነገር ከህዝብ አይበልጥም ያሉት አስተዳዳሪዋ የህግ አውጭዎች ምክር ቤት እጅ ላይ የሚገኘው ህግ ህዝብ ካልፈለገው ሊሰረዝ እንደሚችል ተናግረዋል።

በከተማዋ ጎዳናዎች ለተቃውሞ የወጣው ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ግን ህጉ ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝና አስተዳዳሪዋም ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ላይ ነው።

ዋና ማዕከሉን ቤጂንግ ያደረገው የቻይና መንግስት ዋነኛ ደጋፊ የሆኑትና “ታጋይዋ” የተሰኙት ቻሪየ ላም በአስተዳደር ብቁ ስለመሆናቸው ይነገራል ሲሉ የዘገቡት ቢቢሲ እና አልጀዚራናቸው።