ደቡብ ኮሪያ እያከናወነች ያለው የጦር ጄት ግዥ አደገኛ ነው ስትል ሰሜን ኮሪያ አወገዘች

ደቡብ ኮሪያ እያከናወነች ያለው የኤፍ-35 የጦር ጄት ግዥ አደደገኛ ነው ስትል ሰሜን ኮሪያ አወገዘች፡፡

ደቡብ ኮሪያ አሜሪካ ሰራሽ ኤፍ 35 ዘመናዊ የጦር ጄት ግዥ እያከናዎነች መሆኑ ሰሜን ኮሪያ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ለማምረትና ሙከራ ላይ እንድታውል የሚያስገድድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ክስተቱ ደቡብ ኮሪያ ሁለቱ ሀገራት በቀጠናው ሰላም ዙሪያ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ ትኩረት ያለመሰጠቷን የሚያሳይ መሆኑን የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በስም ያልተጠቀሰ የምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ጠቅሰው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ደቡብ ኮሪያ ኤፍ -35 አሜሪካ ስሪት ሁለት ዘመናዊ የጦር ጄቶችን በአውሮፓዊያኑ መጋቢት ወር ማስገበቷ የተገለጸ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ ጄቶችም በያዝነው የአውሮፓዊያኑ አመት ታስገባለች ተብሎ ይጠበቃልም ነው የተባለው፡፡

እስከ የአውሮፓዊያኑ 2021 ድረስም 40 ዘመናዊ የጦር አውፕላኖችን ለማስገባት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት መፈራረሟ ተገልጿል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በሶሪያ ልሳነ ምድር የወታደራዊ በላይነቱን ለመውሰድ የምታደርውን ያልተጠበቀ የጦር መሳሪያ ግዥ ለቀጠናው አካባቢ ስጋት እና ሰሜን ኮሪያ በቸልተኝነት የማትመለከተው ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ሰሜን ኮሪያ ራሷን ለመከላከል የሚያስችላትን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ለማልማት እና ሙከራ ለማድረግ እንደምትገደድ በዘገባው ተመላክቷል፡፡ (ምንጭ፡-ሬውተርስ)