አሜሪካ ቱርክን ከኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላን ፕሮግራም አገደች

አሜሪካ ቱርክን ኤፍ-35 ከተሰኘው የተዋጊ አውሮፕላን ፕሮግራም ማገዷን አስታውቃለች።

አሜሪካ ቱርክ በቅርቡ ኤስ-400 የተሰኙ የሚሳኤል መቃዎሚያዎችን ከሩሲያ መግዛቷን ተከትሎ ኤፍ -35 ከተሰኘው የተዋጊ አውሮፕላን ፕሮግራም እንዳትሳተፍ አግዳለች።

ውሳኔው የተላለፈውም ዋሽንግተን  ቱርክ ከሩሲያ የምትገዛውን የሚሳኤል መቃዎሚያ ሂዳት እንድታቋረጥ በተደጋጋሚ ካስጠነቀቀች በኋላ  ነው ተብሏል።

ቱርክ በበኩሏ ከሩሲያ  ጋር የገባቸውን የጦር መሳሪያ ግዥ አጠናክራ ከመቀጠል ባለፈ ኤፍ-400 በተሰኘው የሚሳኤል መቃወሚያ ፕሮግራም በቅንጅት የመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑን አስታውቃለች።

ስለሆነም ቱርክ የቀረበላትን ጥሪ ውድቅ ማድረጓን ተከትሎ አሜሪካና አጋሮቿ ኤፍ -35 ከተሰኘው የተዋጊ አውሮፕላን ፕሮግራም እንዳትሳተፍ ማገዳቸው ተገልጿል።

ለዕገዳው የቀረበው ምክንያትም ቱርክ በጉዳዩ ዙሪያ ከሩሲያ ጋር ያላትን ስምምነት የማታቋርጥ ከሆነ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሚስጢራዊ አሰራሮችን አሳልፋ ትሰጣለች የሚል ነው ።

ኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላን በአሁኑ ወቅት ካሉት ተዋጊ አውሮፕላኖች የተሻለ አቅም ያለው ሲሆን፥መሳሪያውን ኔቶ፣ አሜሪካና እና ሌሎች አጋር ሀገራት ይጠቀሙበታል መረጃዉ የሬውተርስ ነዉ ።