አሜሪካ የጦር መርከቤን ተጠግቷል ያለችውን የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን መምታቷን ገለፀች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  የአሜሪካ ባህር ሃይል የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን በስትሬት ኦርሙዝ መትቶ መጣሉን ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን እንዳልተመታባት ገልፃለች፡፡

ይህን ተከትሎ በሁለቱ አገራት የተፈጠረው ውጥረት እየተባባሰና አገራቱን ወደ ጦርነት እንዳያስገባ ስጋቶች ጨምረዋል፡፡

ሰው አልባ አውሮፕላኑ ወደ አሜሪካ የጦር መርከብ መጠጋቱን ተከትሎ ለመርከቡ ደህንነት ሲባል እርምጃ ተወስዷል ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ ቴሄራን ግን ሰው አልባ አውሮፕላን ስለመመታቱ ምንም መረጃ አልደረሰኝም ብላለች፡፡

አሜሪካ ኢራን ከግንቦት ወር ጀምሮ በአለም የመርከብ መንቀሳቀሻ ቦታ ላይ የሚንቀሳቀሱ ነዳጅ ጫኝ ታንከሮች ላይ ወቀሳ እየሰነዘረች ትገኛለች፡፡

ኢራን ግን ወቀሳው መሰረተ ቢስ ነው ባማለት  የአሜሪካን ወቀሳ አጣጥለዋለች፡፡

በሰኔ ወር ላይ ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መትታ መጣሏ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ